1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:3-7

1 ተሰሎንቄ ሰዎች 4:3-7 አማ05

የእግዚአብሔር ፈቃድ እናንተ እንድትቀደሱና ከዝሙት እንድትርቁ ነው። ከእናንተ እያንዳንዱ ሚስቱን በቅድስናና በክብር ጠብቆ መያዝን ይወቅ። እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ የፍትወት ምኞት አይኑረው። በዚህ ነገር ማንም ሰው አይተላለፍ፤ ሌላ አማኝን አይበድል፤ ከዚህ በፊት እንደ ነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉትን ጌታ ይቀጣቸዋል። እግዚአብሔር የጠራን በቅድስና እንድንኖር ነው እንጂ በርኲሰት እንድንኖር አይደለም።