አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 1:12-18

አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 1:12-18 አማ05

ሐና በዚህ ዐይነት ጸሎትዋን በማስረዘም ብዙ ጊዜ ስለ ቈየች፥ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር፤ ሐና ምንም ድምፅ ሳታሰማ ከንፈርዋን እያንቀሳቀሰች በልብዋ በመናገር ትጸልይ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ዔሊ በመጠጥ የሰከረች መሰለው፤ “እንዲህ ሰክረሽ የምትቈዪው እስከ መቼ ነው? ይህን ስካርሽን ወዲያ አስወግጂ!” አላት። እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፦ “አይደለም ጌታዬ ሆይ! እኔ በጥልቅ ሐዘን ላይ ያለሁ ሰው ነኝ፤ ወይን ጠጅም ሆነ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፤ ነገር ግን ችግሬን ለእግዚአብሔር እያቀረብኩ ነው። እኔን አገልጋይህን እንደማትረባ ሴት አድርገህ አትቊጠረኝ፤ ይህን ያኽል በማስረዘም የጸለይኩት መከራ የበዛብኝ ችግረኛ በመሆኔ ነው።” ዔሊም “በሰላም ሂጂ! የእስራኤል አምልክ የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት። እርስዋም “እኔን አገልጋይህን በጸሎትህ አስበኝ!” አለችው፤ ከዚያም ተነሥታ በመሄድ ምግብ ተመገበች፤ ሐዘንዋንም አቆመች።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}