1 የጴጥሮስ መልእክት 3:3-6

1 የጴጥሮስ መልእክት 3:3-6 አማ05

የእናንተ ውበት ጠጒርን በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና፥ የከበረ ልብስ በመልበስ በውጪ በሚታየው ጌጥ አይሁን። ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን። በቀድሞ ጊዜ ተስፋቸውን በእግዚአብሔር ላይ የጣሉ፥ የተቀደሱ ሴቶች ያጌጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ ለባሎቻቸውም ይታዘዙ ነበር። የታዘዙትም ሣራ አብርሃምን “ጌታዬ!” እያለች ትታዘዝለት እንደ ነበረው ዐይነት ነው፤ እናንተም መልካም የሆነውን ነገር ብታደርጉና አንዳች የሚያስፈራ ነገር ባያስደነግጣችሁ የእርስዋ ልጆች ናችሁ።