1 የጴጥሮስ መልእክት 1:3-8

1 የጴጥሮስ መልእክት 1:3-8 አማ05

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱም የማይጠፋውን፥ የማይበላሸውንና የማያረጀውን ርስት በሰማይ አዘጋጅቶላችኋል። እናንተም በመጨረሻው ቀን ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል። ምንም እንኳ የተለያዩ ፈተናዎች ለጥቂት ጊዜ የሚያስቸግሩአችሁ ቢሆኑ በእርሱ ደስ ይበላችሁ። ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል። ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}