ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤ እርሱም የማይጠፋውን፥ የማይበላሸውንና የማያረጀውን ርስት በሰማይ አዘጋጅቶላችኋል። እናንተም በመጨረሻው ቀን ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል። ምንም እንኳ የተለያዩ ፈተናዎች ለጥቂት ጊዜ የሚያስቸግሩአችሁ ቢሆኑ በእርሱ ደስ ይበላችሁ።
1 የጴጥሮስ መልእክት 1 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 የጴጥሮስ መልእክት 1:3-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች