የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት መግቢያ

መግቢያ
መጽሐፈ ነገሥት ክፍል አንድ፥ በሁለቱ የሳሙኤል መጻሕፍት ተጀምሮ የነበረው የእስራኤል ንጉሣዊ አገዛዝ ታሪክ ተከታይ ነው። መጽሐፉ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ሊመደብ ይችላል፦
1. ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት እግር ተተክቶ የእስራኤልና የይሁዳ ንጉሥ ስለ መሆኑና ስለ አባቱም ስለ ዳዊት ሞት የሚተርክ ነው።
2. የሰሎሞን መንግሥት አቋምና ያከናወናቸውን ሥራዎች የሚገልጥ ታሪክ ሲሆን ከእነዚህም ሥራዎች ጐላ ያለው በኢየሩሳሌም የተገነባው ቤተ መቅደስ ነው።
3. እስራኤል የሰሜንና የደቡብ መንግሥት ተብላ በመጠራት ለሁለት ስለ መከፈልዋና እያንዳንዱም መንግሥት ከክርስቶስ ልደት በፊት እስከ ዘጠነኛው ምእት ዓመት ስላስተዳደሩ ነገሥታት የሚተርክ ነው።
በእነዚህ በሁለቱ መጻሕፍት እያንዳንዱ መሪ የሚፈረድበት ለእግዚአብሔር በሚያሳየው ታማኝነት ደረጃ መጠን ነበር፤ እንዲሁም የየአገሩም ዕድገትና መሳካት የሚለካው በዚሁ መሪዎቹ በሚያሳዩት ታማኝነት መጠን ነበር፤ በሌላ በኩል የባዕድ አምልኮን መከተልና አለመታዘዝ፥ መሪዎቹንም ሆነ ሕዝቡን ወደ ጥፋት ይመራቸው ነበር። የሰሜኑ መንግሥት ነገሥታት በሙሉ በፈተና የወደቁ ሲሆኑ፥ የይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ግን ስለ ክፉዎቹም፥ ስለ ደጎቹም የሚያወሳ ነው።
በመጽሐፈ ነገሥት ክፍል አንድ ውስጥ በጣም ታዋቂ የሆኑት፥ እነዚያ እግዚአብሔርን ወክለው የትንቢት ቃል የሚያስተላልፉትና ሕዝቡም የጣዖትን አምልኮ እንዳይከተልና እግዚአብሔርንም መታዘዝ እምቢ እንዳይል ያስጠነቅቁ የነበሩ ቈራጦች ነቢያት ነበሩ፤ ከእነርሱም በጣም ታዋቂ የነበረው ኤልያስ ሲሆን፥ እርሱ ከባዓል ካህናት ጋር ያደረገው ተገዳድሮት ጭምር ተገልጦአል (ም. 18 ተመልከት)።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
ሀ. የዳዊት ዘመን ፍጻሜ 1፥1—2፥12
ለ. የሰሎሞን መንገሥ 2፥13-46
ሐ. የሰሎሞን አገዛዝ 3፥1—11፥43
1. የመጀመሪያዎቹ ዓመቶች 3፥1—4፥34
2. የቤተ መቅደስ ሥራ 5፥1—8፥66
3. የመጨረሻዎች ዓመቶች 9፥1—11፥43
መ. የተከፋፈለው መንግሥት 12፥1—22፥53
1. የሰሜን ነገዶች ዐመፅ 12፥1—14፥20
2. የይሁዳና የእስራኤል ነገሥታት 14፥21—16፥34
3. ነቢዩ ኤልያስ 17፥1—19፥21
4. የእስራኤሉ ንጉሥ አክዓብ 20፥1—22፥40
5. የይሁዳው የንጉሥ ኢዮሣፍጥና የእስራኤሉ ንጉሥ አካዝያስ 22፥41-53

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ