አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:41-44

አንደኛ መጽሐፈ ነገሥት 18:41-44 አማ05

ከዚህ በኋላ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን “እንግዲህ ሄደህ እህልና ውሃ ቅመስ፤ እኔ አሁን የከባድ ዝናም ነጐድጓድ ድምፅ መቃረቡን እየሰማሁ ነው” አለው፤ አክዓብ እህልና ውሃ ለመቅመስ ሲሄድ፥ ኤልያስ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ እዚያም በሁለቱ ጒልበቶቹ መካከል ራሱን ወደ መሬት ደፋ፤ አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤ በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው።