አብ የዓለም አዳኝ አድርጎ ወልድን እንደ ላከው አይተናል፤ እንመሰክራለንም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚያምን ሰው ውስጥ እግዚአብሔር ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል። ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ እናምናለንም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። በዚህ ዓለም እኛ የምንኖረው ልክ ክርስቶስ እንደሚኖረው እንደ መሆኑ ፍቅራችን ፍጹም ቢሆን በፍርድ ቀን ያለ ፍርሀት በፊቱ ለመቅረብ ሙሉ መተማመን ይኖረናል። ፍጹም ፍቅር ፍርሀትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሀት የለም፤ ፍርሀት ከቅጣት ጋር የተያያዘ ስለ ሆነ የሚፈራ ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። እግዚአብሔር አስቀድሞ ስላፈቀረን እኛም እናፈቅራለን።
1 የዮሐንስ መልእክት 4 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 የዮሐንስ መልእክት 4:14-19
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos