ዓለምን ወይም የዓለምን ነገር ሁሉ አትውደዱ። ዓለምን የሚወድ እግዚአብሔር አብን አይወድም። በዓለም ያለው ሁሉ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን አምሮት፥ የኑሮ ትምክሕት ከዓለም ነው እንጂ ከእግዚአብሔር አብ አይደለም። ዓለምና ምኞቱም ያልፋሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘለዓለም ይኖራል። ልጆቼ ሆይ! ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ “የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል” ሲባል ሰምታችኋል፤ እነሆ፥ አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ በዚህ ምክንያት የመጨረሻው ሰዓት መሆኑን እናውቃለን። እነርሱ የወጡት ከእኛ መካከል ነው። ይሁን እንጂ ዱሮውንም ከእኛ ወገን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋርም ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከእኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል። እናንተ ግን ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ቀብቶአችኋል። ስለዚህ ሁላችሁም ሁሉን ነገር ታውቃላችሁ።
1 የዮሐንስ መልእክት 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: 1 የዮሐንስ መልእክት 2:15-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች