1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:4-6

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:4-6 አማ05

ንግግሬና ስብከቴ በሰብአዊ ጥበብና ንግግር በማሳመር ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ኀይል የተደገፈ ነበር። ይህንንም ያደረግኹት እምነታችሁ በሰው ጥበብ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በእግዚአብሔር ኀይል የተደገፈ እንዲሆን ነው። ነገር ግን በመንፈሳዊ ሕይወት ለበሰሉት በጥበብ ቃል እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የምንናገረው የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም መጨረሻቸው ጥፋት የሚሆነውን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም።