1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:27-32

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:27-32 አማ05

ማንም ሰው ያልተገባው ሆኖ ሳለ የጌታን ኅብስት ቢበላና የጌታንም ጽዋ ቢጠጣ የጌታን ሥጋና ደም በማቃለሉ ይጠየቅበታል። ስለዚህ ማንም ሰው ይህን ኅብስት ከመብላቱና ይህንንም ጽዋ ከመጠጣቱ በፊት ራሱን መመርመር አለበት። ማንም ሰው የጌታ ሥጋ ምን መሆኑን ለይቶ ሳያውቅ የጌታን ኅብስት ቢበላና የጌታን ጽዋ ቢጠጣ በራሱ ላይ ፍርድን ያመጣል። ከእናንተ መካከል ብዙዎች የደከሙትና የታመሙት አንዳንዶችም የሞቱት በዚሁ ምክንያት ነው። በራሳችን ላይ ፈርደን ቢሆን ኖሮ ባልተፈረደብንም ነበር። ነገር ግን በኋላ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን አሁን ፈርዶ ጌታ ይገሥጸናል።