1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:1-3

1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:1-3 አማ05

በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ለመሆን ከተጠራው ከጳውሎስና ከወንድማችንም ከሶስቴንስ፦ በቆሮንቶስ ከተማ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በውስጥዋም በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱትና ቅዱሳን እንዲሆኑ ለተጠሩት፥ እንደዚሁም በየቦታው ለእነርሱና ለእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ለሚጠሩት ሁሉ። ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።