ሌሊቱን ሙሉ በዐልጋዬ ላይ ሆኜ፣ ውዴን ተመኘሁ፤ ተመኘሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም። ተነሥቼ ወደ ከተማዪቱ እወጣለሁ፤ በዋና ዋና መንገዶችና በአደባባዮች እዘዋወራለሁ፤ ውዴንም እፈልገዋለሁ፤ ስለዚህም ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም። በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ የከተማዪቱ ጠባቂዎች አገኙኝ፤ እኔም፣ “ውዴን አይታችኋል?” አልኋቸው። ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣ ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤ ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣ በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝ እስካገባው ድረስ አልለቀውም። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣ በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማፅናችኋለሁ።
ማሕልየ መሓልይ 3 ያንብቡ
ያዳምጡ ማሕልየ መሓልይ 3
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማሕልየ መሓልይ 3:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች