ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሧልና። የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ፣ የእርሱም ሙሽራ ራሷን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ፤ ክብርም እንስጠው። የሚያንጸባርቅና ንጹሕ፣ ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ እንድትለብስ ተሰጣት።” ከተልባ እግር የተሠራው ቀጭን ልብስ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው። መልአኩም፣ “ ‘ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው’ ብለህ ጻፍ” አለኝ፤ ቀጥሎም፣ “እነዚህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃሎች ናቸው” አለኝ።
ራእይ 19 ያንብቡ
ያዳምጡ ራእይ 19
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ራእይ 19:6-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos