ከዚህ በኋላ የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ማዳን፣ ክብርና ኀይል የአምላካችን ነው፤ ፍርዱ እውነትና ጽድቅ ነውና፤ በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን፣ ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባታል፤ ስለ ባሮቹም ደም ተበቅሏታል።” ደግሞም እንዲህ አሉ፤ “ሃሌ ሉያ! ጢስ ከርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።” ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ ወድቀው ሰገዱ፤ እንዲህም አሉ፤ “አሜን፣ ሃሌ ሉያ!” ከዚህ በኋላ እንዲህ የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ፤ “እናንተ ባሮቹ ሁሉ፣ እርሱን የምትፈሩ፣ ታናናሾችና ታላላቆችም፣ አምላካችንን አመስግኑ!” ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሧልና። የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ፣ የእርሱም ሙሽራ ራሷን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ፤ ክብርም እንስጠው። የሚያንጸባርቅና ንጹሕ፣ ከተልባ እግር የተሠራ ቀጭን ልብስ እንድትለብስ ተሰጣት።” ከተልባ እግር የተሠራው ቀጭን ልብስ የቅዱሳን የጽድቅ ሥራ ነው። መልአኩም፣ “ ‘ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው’ ብለህ ጻፍ” አለኝ፤ ቀጥሎም፣ “እነዚህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃሎች ናቸው” አለኝ። እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋራ አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አለኝ።
ራእይ 19 ያንብቡ
ያዳምጡ ራእይ 19
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ራእይ 19:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos