የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ራእይ 14:14-19

ራእይ 14:14-19 NASV

አየሁም፤ እነሆ፤ በፊቴ ነጭ ደመና ነበረ፤ በደመናውም ላይ፣ “የሰውን ልጅ የሚመስል” ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በራሱ ላይ የወርቅ አክሊል ደፍቶ፣ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር። ሌላም መልአክ ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፣ “የዐጨዳው ሰዓት ስለ ደረሰ፣ ማጭድህን ይዘህ ዕጨድ፤ የምድር መከር ደርሷልና” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ስለዚህ በደመናው ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደ፤ ምድርም ታጨደች። ሌላም መልአክ በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም እንዲሁ ስለታም ማጭድ ነበረው፤ በእሳት ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ የያዘውን፣ “ዘለላው ስለ በሰለ፣ ስለታም ማጭድህን ያዝና በምድር ላይ ያሉትን የወይን ዘለላዎች ሰብስብ” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ። መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደ፤ የምድርን የወይን ዘለላዎች ሰብስቦ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር የቍጣ ወይን መጭመቂያ ጣላቸው።