መዝሙር 92:12-14

መዝሙር 92:12-14 NASV

ጻድቃን እንደ ዘንባባ ይንሰራፋሉ፤ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይንዠረገጋሉ። በእግዚአብሔር ቤት ተተክለዋል፤ በአምላካችንም አደባባይ ይንሰራፋሉ። ባረጁ ጊዜ እንኳ ያፈራሉ፤ እንደ ለመለሙና እንደ ጠነከሩም ይኖራሉ።