በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል። እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ። እርሱ ከዐዳኝ ወጥመድ፣ ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና። በላባዎቹ ይጋርድሃል፤ በክንፎቹ ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፤ ታማኝነቱ ጋሻና መከታ ይሆንሃል። የሌሊትን አስደንጋጭነት፣ በቀን የሚወረወረውንም ፍላጻ አትፈራም፤ በጨለማ የሚያደባ ቸነፈር፣ በቀትር ረፍራፊውም አያሠጋህም። በአጠገብህ ሺሕ፣ በቀኝህም ዐሥር ሺሕ ይወድቃል፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤ የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ። “እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣” ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።
መዝሙር 91 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 91
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 91:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos