የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 84:1-4

መዝሙር 84:1-4 NASV

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ማደሪያህ ምንኛ የተወደደ ነው! ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትናፍቃለች፤ እጅግም ትጓጓለታለች፤ ልቤና ሥጋዬም፣ ለሕያው አምላክ እልል በሉ። ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህ ባለበት ስፍራ፣ ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት፣ ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ጐጆ አገኘች። ብፁዓን ናቸው፤ በቤትህ የሚኖሩ፣ እነርሱም ለዘላለም ያመሰግኑሃል። ሴላ