እግዚአብሔር ልባቸው ንጹሕ ለሆነ፣ ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው! እኔ ግን እግሬ ሊሰናከል፣ አዳልጦኝም ልወድቅ ጥቂት ቀረኝ። ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣ በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና። አንዳች ጣር የለባቸውም፤ ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው። በሰዎች የሚደርሰው ጣጣ አይደርስባቸውም፤ እንደ ማንኛውም ሰው መከራ አያገኛቸውም። ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል። የሠባ ዐይናቸው ይጕረጠረጣል፤ ልባቸውም በከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይፈስሳል። በፌዝና በክፋት ይናገራሉ፤ ቀና ቀና ብለውም በዐመፅ ይዝታሉ። አፋቸውን በሰማይ ላይ ያላቅቃሉ፤ አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል። ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይነጕዳል፤ ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ። “ለመሆኑ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ ዕውቀት አለ?” ይላሉ። እንግዲህ፣ ክፉዎች ይህን ይመስላሉ፤ ሁልጊዜ ግድ የለሽና ሀብት በሀብት ናቸው። ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤ እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሯል! ቀኑን ሙሉ ተቀሠፍሁ፤ ጧት ጧትም ተቀጣሁ።
መዝሙር 73 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 73
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 73:1-14
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos