ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ነውና። ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም። መዳኔና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ ብርቱ ዐለቴና መሸሸጊያዬ በእግዚአብሔር ነው። ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፤ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ ከተናቀ ወገን መወለድ ከንቱ፣ ከከበረውም መወለድ ሐሰት ነው። በሚዛን ላይ ከፍ ብለው ቢታዩም፣ ሁሉም በአንድነት ከነፋስ የቀለሉ ናቸው።
መዝሙር 62 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 62
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 62:5-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos