ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም። ክንድህን አንሣልኝ፤ ከእጅህ ምት የተነሣ ደክሜአለሁ። ሰዎችን ስለ ኀጢአታቸው ለመቅጣት ትገሥጻቸዋለህ፤ ሀብታቸውንም ብል እንደ በላው ታደርጋለህ፤ በርግጥ ሰው ሁሉ ተን ብቻ ነው። ሴላ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴን አድምጥ፤ ልቅሶዬንም ቸል አትበል፤ በአንተ ፊት እኔ መጻተኛ ነኝና፤ እንደ አባቶቼም እንግዳ ነኝ። ላለመመለስ ከመሰናበቴ በፊት፣ ዳግመኛ ደስ ይለኝ ዘንድ ዐይንህን ከላዬ አንሣ።”
መዝሙር 39 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 39
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 39:9-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos