እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ። ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ። የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤ እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ። የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው። የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል። ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣ ሢርዮንንም እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል። የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል። የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤ የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል። የእግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤ ጫካዎችንም ይመነጥራል፤ ሁሉም በርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል። እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል፤ እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።
መዝሙር 29 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 29
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 29:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos