የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 24

24
መዝሙር 24
ወደ መቅደስ መግቢያ ጸሎት
የዳዊት መዝሙር።
1ምድርና በእርሷ ያለው ሁሉ፣
ዓለምና በውስጧ የሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤
2እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤
በውሆችም ላይ አጽንቷታል።
3ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ሊወጣ ይችላል?
በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
4ንጹሕ እጅና ቅን ልብ ያለው፤
ነፍሱን ለሐሰት ነገር የማያስገዛ፤
በውሸት የማይምል፤#24፥4 ወይም በሐሰትም ያልማለ
5እርሱ በረከትን ከእግዚአብሔር ዘንድ፣
ምሕረትንም ከአዳኝ አምላኩ ይቀበላል።
6እርሱን የሚፈልግ ትውልድ እንዲህ ነው፤
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፤ ፊትህን#24፥6 ሁለት የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆችና ሱርስት (እንዲሁም ሰብዓ ሊቃናትን ይመ) እንዲሁ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች ግን ያዕቆብ፤ ፊትህን… የሚፈልግ እንዲህ ያለ ነው። ሴላ
7እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤
እናንተ የዘላለም በሮች፤
የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
8ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
እግዚአብሔር ነው ብርቱና ኀያል፤
እግዚአብሔር ነው በውጊያ ኀያል።
9እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤
እናንተ የዘላለም በሮች፤
የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ!
10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
የሰራዊት አምላክ
እርሱ የክብር ንጉሥ ነው። ሴላ

Currently Selected:

መዝሙር 24: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ