መዝሙር 22:12-21

መዝሙር 22:12-21 NASV

ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤ ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ። እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ፣ አፋቸውን ከፈቱብኝ። እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ። ጕልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤ ምላሴ ከላንቃዬ ጋራ ተጣበቀ፤ ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ። ውሾች ከበቡኝ፤ የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፏል፤ እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ። ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤ እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል። ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ። አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤ ዐጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን። ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤ ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት። ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤ ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።