ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ። ቀን ለሌላው ቀን ይናገራል፤ ሌሊትም ለሌሊት ዕውቀትን ይገልጣል፤ ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም። ያም ሆኖ ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፣ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ይወጣል። እርሱ በሰማያት ለፀሓይ ድንኳን ተክሏል፤ ፀሓይም ከእልፍኙ እንደሚወጣ ሙሽራ ይወጣል፤ ወደ ግቡም እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል። መውጫው ከሰማያት ዳርቻ ነው፤ ዑደቱም እስከ ሌላኛው ዳርቻ ነው፤ ከትኵሳቱም የሚሰወር የለም።
መዝሙር 19 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 19
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 19:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos