መዝሙር 18:30-35

መዝሙር 18:30-35 NASV

የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ፣ ጋሻ ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው? ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ እግዚአብሔር ነው። እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል። እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ። የማዳንህን ጋሻ ሰጥተኸኛል፤ ቀኝ እጅህም ደግፋ ይዛኛለች፤ ድጋፍህ ታላቅ አድርጎኛል።