እግዚአብሔር ሆይ፤ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰው ኰረብታህስ ማን መኖር ይችላል? አካሄዱ የቀና፣ ጽድቅን የሚያደርግ፤ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤ በምላሱ የማይሸነግል፤ በባልንጀራው ላይ ክፉ የማይሠራ፤ ወዳጁን የማያማ፤ ነውረኛ በፊቱ የተናቀ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፤ ዋጋ የሚያስከፍለውም ቢሆን፣ ቃለ መሐላውን የሚጠብቅ፤ ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር፣ በንጹሓን ላይ ጕቦ የማይቀበል።
መዝሙር 15 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 15
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 15:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos