የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 147

147
መዝሙር 147
መዝሙር ለሁሉን ቻይ አምላክ
1ሃሌ ሉያ።#147፥1 አንዳንዶች ከ20 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።
አምላካችንን በመዝሙር ማወደስ እንዴት መልካም ነው!
እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ይህ ተገቢም ነው።
2 እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤
ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል።
3ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤
ቍስላቸውንም ይጠግናል።
4የከዋክብትን ብዛት ያውቃል፤
እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል።
5ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤
ለጥበቡም ወሰን የለውም።
6 እግዚአብሔር ትሑታንን ከፍ ያደርጋል፤
ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል።
7 ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤
ለአምላካችንም በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።
8ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤
ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤
በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል።
9ለእንስሳት ምግባቸውን፣
የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።
10እርሱ በፈረስ ኀይል አይደሰትም፤
በሯጭም ብርታት ላይ ደስታውን አያደርግም።
11ነገር ግን እግዚአብሔር በሚፈሩት፣
በምሕረቱ በሚታመኑትም ይደሰታል።
12ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እግዚአብሔርን አመስግኚ፤
ጽዮን ሆይ፤ አምላክሽን አወድሺ፤
13እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤
ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኳል።
14በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤
ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል።
15ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤
ቃሉም እጅግ በፍጥነት ይሮጣል።
16ዐመዳዩን እንደ በርኖስ ይዘረጋል፤
ውርጩን እንደ ዐመድ ይነሰንሳል።
17የበረዶውን ድንጋይ ቍልቍል ይወረውረዋል፤
በውሽንፍሩስ ቅዝቃዜ ፊት ማን ሊቆም ይችላል?
18ቃሉን ልኮ ያቀልጣቸዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፤ ውሆችንም ያፈስሳል።
19ቃሉን ለያዕቆብ፣
ሥርዐቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይገልጣል።
20ይህን ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ አላደረገም፤
እነርሱም ፍርዱን አላወቁም።
ሃሌ ሉያ።

Currently Selected:

መዝሙር 147: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ