መዝሙር 141
141
መዝሙር 141
የክፉዎችን ድሎት ላለመመኘት የቀረበ ጸሎት
የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤
ወደ አንተ ስጣራም ድምፄን ስማ።
2ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ትቈጠርልኝ፤
እጄን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን።
3 እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤
የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
4ከዐመፀኞች ጋር፣
በክፉ ሥራ እንዳልተባበር፣
ልቤን ወደ ክፉ አታዘንብል፤
ከድግሳቸውም አልቋደስ።
5ጻድቅ#141፥5 ወይም ጻድቁ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤
ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤
ራሴም ይህን እንቢ አይልም።
ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው፤
6ሹማምታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፤
ቃሌ የምታረካ ናትና ይሰሟታል።
7ደግሞም፣ “ሰው ምድርን እንደሚያርስና ዐፈሩን እንደሚፈረካክስ፣
እንዲሁ ዐጥንታችን በሲኦል#141፥7 አንዳንድ ትርጕሞች መቃብር ይላሉ። አፋፍ ላይ ተበታተነ” ይላሉ።
8ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ፤
መጠጊያዬም አንተ ነህ፤ እንግዲህ ነፍሴን አትተዋት።
9ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣
ከክፉ አድራጊዎችም አሽክላ ጠብቀኝ።
10እኔ ብቻ በደኅና ሳመልጥ፣
ክፉዎቹ በገዛ ወጥመዳቸው ይውደቁ።
Currently Selected:
መዝሙር 141: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.