እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ድረስ ነው? ከሐሳቤ ጋራ የምሟገተው፣ ልቤም ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው? ጠላቴስ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ድረስ ነው? እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ ስማኝም። የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤ በዚህም ጠላቴ፣ “አሸነፍሁት” እንዳይል፣ ባላጋራዎቼም በውድቀቴ ደስ እንዳይላቸው ርዳኝ። እኔ ግን በጸናች ፍቅርህ እታመናለሁ፤ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል። ቸርነቱ ታምኛለሁና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።
መዝሙር 13 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 13
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 13:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos