መዝሙር 128:1-6

መዝሙር 128:1-6 NASV

ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣ በመንገዱም የሚሄዱ፤ የድካምህን ፍሬ ትበላለህ፤ ብፅዕና እና ብልጽግና የአንተ ይሆናሉ። ሚስትህ በቤትህ፣ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ወንዶች ልጆችህ በማእድህ ዙሪያ፣ እንደ ወይራ ተክል ናቸው። እነሆ፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው፣ እንዲህ ይባረካል። እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፤ የልጅ ልጅ ለማየትም ያብቃህ።