መዝሙር 119:33-40

መዝሙር 119:33-40 NASV

እግዚአብሔር ሆይ፤ የሥርዐትህን መንገድ አስተምረኝ፤ እኔም እስከ መጨረሻው እጠብቀዋለሁ። ሕግህን እንድጠብቅ፣ በፍጹም ልቤም እንድታዘዘው፣ ማስተዋልን ስጠኝ። በርሷ ደስ ይለኛልና፣ በትእዛዝህ መንገድ ምራኝ። ከራስ ጥቅም ይልቅ፣ ልቤን ወደ ምስክርነትህ አዘንብል። ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ፤ በራስህ መንገድ እንደ ገና ሕያው አድርገኝ። ትፈራ ዘንድ፣ ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ፈጽም። የምፈራውን መዋረድ ከእኔ አርቅ፤ ደንብህ መልካም ነውና። እነሆ፤ ድንጋጌህን ናፈቅሁ፤ በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ።