የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 113

113
መዝሙር 113
ለታላቁና ለመሓሪው ጌታ ምስጋና
1ሃሌ ሉያ።#113፥1 እግዚአብሔር ይመስገን ማለት ሲሆን፣ በ9 ላይም ይገኛል።
የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሆይ፤ አመስግኑት፤
የእግዚአብሔርን ስም አወድሱ።
2ከአሁን እስከ ዘላለም፣
የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
3ከፀሓይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ፣
የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን።
4 እግዚአብሔር ከሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤
ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር
በላይ በዙፋኑ የተቀመጠ ማን ነው?
6በሰማይና በምድር ያሉትንስ ለማየት፣
ራሱን ወደ ታች ዝቅ የሚያደርግ ማን ነው?
7ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤
ችግረኛውን ከዐመድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤
8ከመኳንንትም እኩል ስፍራ ይሰጠዋል፤
ከሕዝቡም ሹማምት ጋር ያስቀምጠዋል።
9መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤
ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል።
ሃሌ ሉያ።

Currently Selected:

መዝሙር 113: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ