አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ ለዐፈሯም ይሳሳሉ። ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣ የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ። እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤ በክብሩም ይገለጣል። እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም። ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ ይህ ለመጭው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤ “እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቷልና፤ ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቷል፤ ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።” ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣ ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤ ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል። ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤ ዕድሜዬንም በዐጭሩ አስቀረው። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ፤ ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ። አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም። የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤ ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”
መዝሙር 102 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 102
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 102:14-28
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos