በቤቴ መስኮት፣ በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ። ልበ ቢሱን ወጣት፣ ከአላዋቂዎች መካከል አየሁት፤ ከጕልማሶችም መካከል ለየሁት። የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣ በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤ ቀኑ መሸትሸት ሲል፣ በውድቅት ሌሊት፣ በጽኑ ጨለማ። ከዚያም አንዲት ሴት ልታገኘው ወጣች፤ እንደ ዝሙት ዐዳሪ ለብሳ፣ ለማሳሳት ታጥቃ። ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ናት፤ እግሮቿ ዐርፈው ቤት አይቀመጡም፤ አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ፣ በየማእዘኑም ታደባለች። አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ ኀፍረቷንም ጥላ እንዲህ አለችው፤ “በቤቴ የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ፤ ስለዚህ አንተን ለማግኘት ወጣሁ፤ ፈልጌህ ነበር፤ ይኸው አገኘሁህ። ዐልጋዬን ከግብጽ የመጣ፣ ጌጠኛ በፍታ አልብሼዋለሁ። ዐልጋዬን፣ የከርቤ፣ የአደስና የቀረፋ ሽቱ አርከፍክፌበታለሁ። ና፤ እስኪነጋ በጥልቅ ፍቅር እንርካ፤ በፍቅር ራሳችንን እናስደስት። ባሌ እቤት የለም፤ ሩቅ አገር ሄዷል። በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን አይመለስም።”
ምሳሌ 7 ያንብቡ
ያዳምጡ ምሳሌ 7
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ምሳሌ 7:6-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos