ምሳሌ 4:5-7

ምሳሌ 4:5-7 NASV

ጥበብን አግኛት፤ ማስተዋልን ያዛት፤ ቃሌን አትርሳ፤ ከርሷም ዘወር አትበል። ጥበብን አትተዋት፤ እርሷም ከለላ ትሆንሃለች፤ አፍቅራት፤ እርሷም ትጠብቅሃለች። ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤ ያለህን ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት።