ክፉ ሰው ማንም ሳያሳድደው ይሸሻል፤ ጻድቅ ግን እንደ አንበሳ ልበ ሙሉ ነው። አገር ስታምፅ፣ ገዦቿ ይበዛሉ፤ አስተዋይና ዐዋቂ ሰው ግን ሥርዐትን ያሰፍናል። ድኾችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ ሰብል እንደሚያጠፋ ኀይለኛ ዝናብ ነው። ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል። ክፉዎች ፍትሕን አያስተውሉም፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን ሙሉ በሙሉ ያውቁታል። በአካሄዱ ነውር የሌለበት ድኻ፣ መንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይሻላል። ሕግን የሚጠብቅ አስተዋይ ልጅ ነው፤ ከሆዳሞች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን አባቱን ያዋርዳል።
ምሳሌ 28 ያንብቡ
ያዳምጡ ምሳሌ 28
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ምሳሌ 28:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos