የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ምሳሌ 1:8-19

ምሳሌ 1:8-19 NASV

ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤ የእናትህንም ትምህርት አትተው። ለራስህ ሞገስን የሚያጐናጽፍ አክሊል፣ ዐንገትህን የሚያስውብ ድሪ ይሆንልሃል። ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣ እሺ አትበላቸው፤ “ከእኛ ጋር ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤ በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤ እንደ መቃብር፣ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው እንዳሉ እንዋጣቸው፤ ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በየዐይነቱ እናገኛለን፤ ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤ ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል፤ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል” ቢሉህ፣ ልጄ ሆይ፤ አብረሃቸው አትሂድ፤ በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤ እግራቸው ወደ ኀጢአት ይቸኵላል፤ ደም ለማፍሰስም ፈጣኖች ናቸው። ወፎች ፊት እያዩ ወጥመድ መዘርጋት፣ ምንኛ ከንቱ ነው! እነዚህ ሰዎች የሚያደቡት በገዛ ደማቸው ላይ ነው፤ የሚሸምቁትም በራሳቸው ላይ ብቻ ነው። ያላግባብ ለጥቅም የሚሯሯጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ የሕይወታቸው መጥፊያም ይኸው ነው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}