የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

አብድዩ 1:8-14

አብድዩ 1:8-14 NASV

“በዚያ ቀን ጥበበኛ ሰዎችን ከኤዶም፣ አስተዋዮችንም ከዔሳው ተራሮች አልደመስስምን?” ይላል እግዚአብሔር። “ቴማን ሆይ፤ ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ፤ በዔሳውም ተራሮች ያለ ሁሉ፣ ተገድሎ ይጠፋል። በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፣ በዕፍረት ትሸፈናለህ፤ ለዘላለምም ትጠፋለህ። እንግዶች ሀብቱን ዘርፈው ሲሄዱ፣ ባዕዳንም በበሮቹ ሲገቡ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ ሲጣጣሉ፣ በዚያ ቀን ገለልተኛ ሆነህ ተመለከትህ፣ አንተም ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆንህ። ክፉ ቀን በገጠመው ጊዜ፤ በወንድምህ ሥቃይ መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ የይሁዳ ሕዝብ ሲያዝኑ ሐሤት ማድረግ አልነበረብህም፤ በጭንቀታቸውም ቀን፣ በትዕቢት ልትናገር አይገባህም ነበር። በጥፋታቸው ቀን፣ በሕዝቤ በር መግባት የለብህም ነበር፤ በጥፋታቸው ቀን፣ በጭንቀታቸው መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር። ስደተኞቻቸውን ለመግደል፣ በመንታ መንገድ መጠባበቅ አይገባህም ነበር፣ በጭንቀታቸው ቀን፣ የተረፉትን አሳልፈህ መስጠት አልነበረብህም።