የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 13:1-16

ዘኍል 13:1-16 NASV

እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።” ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ፤ ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፤ ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፤ ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካሌብ፤ ከይሳኮር ነገድ፣ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፤ ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፤ ከብንያም ነገድ፣ የራፉ ልጅ ፈልጢ፤ ከዛብሎን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፤ ከምናሴ ነገድ ይህም የዮሴፍ ነገድ ነው፤ የሱሲ ልጅ ጋዲ፤ ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፤ ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፤ ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፤ ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል። እንግዲህ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴ ለነዌ ልጅ ለአውሴ፣ “ኢያሱ” የሚል ስም አወጣለት።