ነህምያ 10
10
1ያተሙትም እነዚህ ናቸው፤
የሐካልያ ልጅ አገረ ገዥው ነህምያ።
ሴዴቅያስ፣ 2ሠራያ፣ ዓዛርያስ፣ ኤርምያስ፣
3ፋስኮር፣ አማርያ፣ መልክያ፣
4ሐጡስ፣ ሰበንያ፣ መሉክ፣
5ካሪም፣ ሜሪሞት፣ አብድዩ፣
6ዳንኤል፣ ጌንቶን፣ ባሮክ፣
7ሜሱላም፣ አብያ፣ ሚያሚን፣
8መዓዝያ፣ ቤልጋይ፣ ሸማያ፤
እነዚህ ካህናት ነበሩ።
9ሌዋውያኑ፦
የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፣ ከኤንሐዳድ ወንዶች ልጆች ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣
10ወንድሞቻቸው፦
ሰባንያ፣ ሆዲያ፣ ቆሊጣስ፣ ፌልያ፣ ሐናን፣
11ሚካ፣ ረአብ፣ ሐሸብያ፣
12ዘኩር፣ ሰራብያ፣ ሰበንያ፣
13ሆዲያ፣ ባኒ፣ ብኒኑ።
14የሕዝብ መሪዎች፦
ፋሮስ፣ ፈሐት፣ ሞዓብ፣ ኤላም፣ ዛቱዕ፣ ባኒ፣
15ቡኒ፣ ዓዝጋድ፣ ቤባይ፣
16አዶንያስ፣ በጉዋይ፣ ዓዲን፣
17አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዙር፣
18ሆዲያ፣ ሐሱም፣ ቤሳይ፣
19ሐሪፍ፣ ዓናቶት፣ ኖባይ፣
20መግጲዓስ፣ ሜሱላም፣ ኤዚር፣
21ሜሴዜቤል፣ ሳዶቅ፣ ያጹአ፣
22ፈላጥያ፣ ሐናን፣ ዓናያ፣
23ሆሴዕ፣ ሐናንያ፣ አሱብ፣
24አሎኤስ፣ ፈልሃ፣ ሶቤቅ፣
25ሬሁም፣ ሐሰብና፣ መዕሤያ፣
26አኪያ፣ ሐናን፣ ዓናን፣
27መሉክ፣ ካሪምና በዓና።
28የቀሩት ሕዝብ፦ ማለት ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑ፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ስለ እግዚአብሔር ሕግ ብለው ራሳቸውን ከጎረቤት አሕዛብ የለዩ ሁሉ፣ ሚስቶቻቸው፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፣ የሚያውቁና የሚያስተውሉ ሁሉ ቃለ መሐላ ፈጸሙ፤ 29እነርሱም ከወንድሞቻቸውና ከመኳንንታቸው ጋር በመሆን በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ የጌታችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች፣ ደንቦችና ሥርዐቶች ሁሉ ለመታዘዝ በዚህ ርግማንና መሐላ ቃል ገቡ።
30“ሴት ልጆቻችንን በዙሪያችን ላሉት አሕዛብ አንሰጥም፤ የእነርሱን ሴቶች ልጆች ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም።
31“አሕዛብ ጎረቤቶቻችን በሰንበት ቀን ለመሸጥ ሸቀጣ ሸቀጥ ወይም እህል ቢያመጡ፣ በሰንበት ወይም በማናቸውም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም። በየሰባት ዓመቱም ምድሪቱን እናሳርፋለን፤ ዕዳንም ሁሉ እንሠርዛለን።
32“በየዓመቱ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት የሚሆን የሰቅል#10፥32 4 ግራም ያህል ነው። አንድ ሦስተኛ ለመስጠት ቃል እንገባለን፤ 33ይህም በጠረጴዛው ላይ ለሚቀርበው ገጸ ኅብስት፣ ዘወትር ለሚቀርበው የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ በሰንበት፣ በወር መባቻና በተደነገጉ በዓላት ለሚቀርበው መሥዋዕት፣ ለተቀደሱ መባዎች፣ ለእስራኤል ስርየት ለሚቀርበው የኀጢአት መሥዋዕትና ለአምላካችን ቤት ሥራ ሁሉ የሚውል ነው።
34“እኛ፣ ማለት ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና ሕዝቡ በየዓመቱ በተወሰነው ጊዜ በሕጉ እንደ ተጻፈው፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚነድደውን ዕንጨት የእያንዳንዳችን ቤተ ሰብ መቼ ወደ አምላካችን ቤት ማምጣት እንዳለበት ለመወሰን ዕጣ ተጣጣልን።
35“የሰብላችንንና የእያንዳንዱን ዛፍ ፍሬ በኵራትም ወደ እግዚአብሔር ቤት ለማምጣት ቃል እንገባለን።
36“እንዲሁም በሕጉ እንደ ተጻፈው የወንድ ልጆቻችንንና፣ የቀንድ ከብቶቻችንን፣ የመንጋዎቻችንን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችንን በኵራት ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደሚያገለግሉትም ካህናት እናመጣለን።
37“ከዚህም በላይ የቡሗችንን፣ የእህል ቍርባናችንን፣ የዛፎቻችንን ፍሬ ሁሉ፣ አዲሱን የወይን ጠጃችንንና የዘይታችንን በኵራት ወደ ካህናቱ፣ ወደ አምላካችን ቤት ዕቃ ቤቶች እናመጣለን። እኛ በምንሠራባቸው ከተሞች ሁሉ ያለውን ዐሥራት የሚሰበስቡት ሌዋውያን ስለሆኑ፣ የሰብላችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያኑ እናመጣለን። 38ዐሥራቱን በሚቀበሉበት ጊዜም ከአሮን ዘር የተወለደው ካህን ከሌዋውያኑ ጋር አብሮ ይገኛል፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን አንድ ዐሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደ ዕቃ ማከማቻ ክፍሎች ያመጡታል። 39የእስራኤል ሕዝብና ሌዋውያኑ ጭምር፣ ከእህሉ፣ ከዐዲሱ ወይን ጠጅና ከዘይቱ ያዋጡትን፣ የመቅደሱ ዕቃዎች ወደሚቀመጡባቸው፣ አገልጋይ ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና መዘምራኑ ወደሚያርፉባቸው ዕቃ ቤቶች ያምጡ።
“እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።”
Currently Selected:
ነህምያ 10: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.