የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሚክያስ 1:8-16

ሚክያስ 1:8-16 NASV

በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤ እንደ ጕጕትም አቃስታለሁ። ቍስሏ የማይሽር ነውና፤ ለይሁዳ ተርፏል፤ እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሷል። በጌት አታውሩት፤ ከቶም አታልቅሱ፤ በቤትዓፍራ፣ በትቢያ ላይ ተንከባለሉ። እናንት በሻፊር የምትኖሩ፣ ዕርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ዕለፉ፤ በጸዓናን የሚኖሩ ከዚያ አይወጡም፤ ቤትዔጼል በሐዘን ላይ ናት፤ ለእናንተም መጠጊያ ልትሆን አትችልም። ከመከራው መገላገልን በመሻት፣ በማሮት የሚኖሩ በሥቃይ ይወራጫሉ፤ እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣ ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷልና። እናንት በለኪሶ የምትኖሩ፣ ፈረሶችን ከሠረገላው ጋር አያይዙ፤ ለጽዮን ሴት ልጅ፣ የኀጢአት መጀመሪያ እናንት ነበራችሁ፤ የእስራኤል በደል በእናንተ ዘንድ ተገኝቷልና። ስለዚህ እናንተ ለሞሬሼትጌት፣ ማጫ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብ ከተማ፣ ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ትሆናለች። እናንት በመሪሳ የምትኖሩ ድል አድራጊ አመጣባችኋለሁ፤ ያ የእስራኤል ክብር የሆነው ወደ ዓዶላም ይመጣል። ደስ ለምትሰኙባቸው ልጆቻችሁ፣ በሐዘን ራሳችሁን ተላጩ፤ ራሳችሁን እንደ አሞራ ራስ ተመለጡት፤ ከእናንተ በምርኮ ይወሰዳሉና።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}