ከዚያም የአገረ ገዥው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዥው ግቢ ወሰዱት፤ ሰራዊቱንም ሁሉ በዙሪያው አሰባሰቡ። ልብሱን ገፍፈው ቀይ ልብስ አጠለቁለት፤ እሾኽ ጐንጕነው አክሊል በመሥራት ራሱ ላይ ደፉበት፤ የሸንበቆ በትር በቀኝ እጁ በማስያዝ በፊቱ ተንበርክከው፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን” በማለት አሾፉበት፤ ተፉበትም፤ የሸንበቆ በትሩን ከእጁ ወስደው ራሱ ላይ በሸንበቆው ደግመው ደጋግመው መቱት፤ ካሾፉበት በኋላም ቀዩን ልብስ ገፍፈው የራሱን መጐናጸፊያ አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ይዘውት ሄዱ።
ማቴዎስ 27 ያንብቡ
ያዳምጡ ማቴዎስ 27
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማቴዎስ 27:27-31
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos