ጧት በማለዳ ላይ፣ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስ ስለሚገደልበት ሁኔታ ተመካከሩ፤ ካሰሩትም በኋላ ወስደው ለገዥው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ ተጸጸተ፤ የወሰደውን ሠላሳ ጥሬ ብር ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ ሽማግሌዎች መልሶ በመስጠት፣ “ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ” አለ። እነርሱም፣ “ታዲያ እኛ ምን አገባን፤ የራስህ ጕዳይ ነው!” አሉት። ስለዚህ ይሁዳ ብሩን በቤተ መቅደስ ውስጥ ወርውሮ ወጣ፤ ሄዶም ራሱን ሰቅሎ ሞተ። የካህናት አለቆች ብሩን አንሥተው፣ “የደም ዋጋ ስለሆነ ወደ መባ ልንጨምረው አይፈቀድም” አሉ፤ ተመካክረውም ለእንግዶች የመቃብር ስፍራ እንዲሆን በገንዘቡ የሸክላ ሠሪውን ቦታ ገዙበት።
ማቴዎስ 27 ያንብቡ
ያዳምጡ ማቴዎስ 27
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማቴዎስ 27:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos