የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ማቴዎስ 15:1-11

ማቴዎስ 15:1-11 NASV

ከዚያም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ “ደቀ መዛሙርትህ የአባቶችን ወግ የሚተላለፉት ለምንድን ነው? ምግብ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡም” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እናንተስ ለወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትሽራላችሁ? እግዚአብሔር፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል’ ብሎ ሲያዝዝ፣ እናንተ ግን፣ ማንም ሰው አባቱን ወይም እናቱን፣ ‘ከእኔ ማግኘት የሚገባችሁን ርዳታ ሁሉ ለእግዚአብሔር መባ እንዲሆን ሰጥቻለሁ’ ቢላቸው፣ ‘አንድ ሰው ይህን ካደረገ አባቱን ወይም እናቱን አክብሯል’ ትላላችሁ። ስለዚህ ለወጋችሁ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ። እናንተ ግብዞች፤ ኢሳይያስ ስለ እናንተ እንዲህ ብሎ በትንቢት የተናገረው ትክክል ነው፤ “ ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በከንቱ ያመልኩኛል፣ ትምህርታቸውም ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው።’ ” ሕዝቡን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ስሙ፤ አስተውሉም፤ ሰውን የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው እንጂ ወደ አፉ የሚገባው አይደለም።”

ተዛማጅ ቪዲዮዎች