ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበት መጣ። ደቀ መዛሙርቱም በባሕሩ ላይ እየተራመደ ሲመጣ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ምትሀት ነው!” በማለት በፍርሀት ጮኹ። ኢየሱስም ወዲያውኑ፣ “አይዟችሁ፤ እኔ ነኝ አትፍሩ” አላቸው። ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ከሆንህስ፣ በውሃው ላይ እየተራመድሁ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ” አለው። እርሱም፣ “ና” አለው። ጴጥሮስም፣ ከጀልባው ወርዶ በውሃው ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ አመራ።
ማቴዎስ 14 ያንብቡ
ያዳምጡ ማቴዎስ 14
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማቴዎስ 14:25-29
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos