ሰልሞን ቦዔዝን ከረዓብ ወለደ፤ ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ። ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችው ሰሎሞንን ወለደ፤ ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤ አሣፍ ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥ ይሆራምን ወለደ፤ ይሆራም ዖዝያንን ወለደ፤ ዖዝያን ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታም አካዝን ወለደ፤ አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤ ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤ ምናሴ አሞንን ወለደ፤ አሞንም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ፣ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ። ከባቢሎን ምርኮ በኋላ፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤ ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤ አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄም አዛርን ወለደ፤ አዛር ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤ ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛር ማታንን ወለደ፤ ማታን ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ዮሴፍን ወለደ፤ ዮሴፍም የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የማርያም ዕጮኛ ነበር። እንግዲህ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ዐሥራ አራት ትውልድ፣ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ዐሥራ አራት ትውልድ፣ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ልደት ዐሥራ አራት ትውልድ ይሆናል።
ማቴዎስ 1 ያንብቡ
ያዳምጡ ማቴዎስ 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማቴዎስ 1:5-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች