የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሉቃስ 23:50-56

ሉቃስ 23:50-56 NASV

የአይሁድ ሸንጎ አባል የሆነ፣ አንድ ዮሴፍ የሚባል በጎና ጻድቅ ሰው ነበር። ይህ ሰው በሸንጎው ምክርና ድርጊት አልተባበረም ነበር፤ እርሱም አርማትያስ የምትባል የአይሁድ ከተማ ሰው ሲሆን፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መምጣት ይጠባበቅ ነበር። ይህም ሰው ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው፤ በተፈቀደለትም ጊዜ፣ ሥጋውን አውርዶ በበፍታ ከፈነው፤ ከድንጋይ ተፈልፍሎ በተሠራና ገና ማንም ባልተቀበረበት መቃብር ውስጥ አስቀመጠው። ዕለቱ ሰንበት ሊገባ ስለ ነበር፣ የመዘጋጃ ቀን ነበረ። ከገሊላ ጀምሮ ከኢየሱስ ጋራ የመጡት ሴቶችም ተከትለው መቃብሩን አዩ፤ ሥጋውንም እንዴት እንዳስቀመጡት ተመለከቱ። ከዚያም ተመልሰው ሽቱና ቅባት አዘጋጁ፤ ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት በሰንበት ቀን ዐረፉ።