እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ባይታመን፤ ከተቀደሰ ከማናቸውም ነገር በማጕደል ኀጢአት ቢሠራ፣ ከመንጋው እንከን የሌለበትን አውራ በግ የበደል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ። የዋጋውም ግምት በቤተ መቅደሱ ሰቅል መሠረት ተመዝኖ በጥሬ ብር ይሁን፤ ይህም የበደል መሥዋዕት ነው። ከተቀደሱ ነገሮች ያጐደለውንም ይተካ፤ የዚህንም ተመን አንድ ዐምስተኛ በላዩ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፤ ካህኑም ከበጉ ጋራ የበደል መሥዋዕት አድርጎ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል። “ማንኛውም ሰው ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ከከለከላቸው ትእዛዞች ሳያውቅ አንዱን ተላልፎ ቢገኝ በደለኛ ነው፤ በኀጢአቱም ይጠየቅበታል። እርሱም ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት የሚሆን እንከን የሌለበት አውራ በግ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ዋጋውም ተመጣጣኝ ይሁን። ካህኑም በዚህ ሁኔታ ሰውየው ሳያውቅ ስለ ፈጸመው ስሕተት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል። ይህ የበደል መሥዋዕት ነው። ሰውየውም በእግዚአብሔር ፊት ጥፋት በመፈጸሙ በደለኛ ነው።”
ዘሌዋውያን 5 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘሌዋውያን 5
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘሌዋውያን 5:14-19
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos